Explore
Also Available in:

ድንጋዮች እና አጥንቶች

የዝግመተ-ስዉጥ ሽክስተሳሰብ ሲፈተሽ

Carl Wieland

በእውኑ የዝግመተ-ለውጥ (evolution) አመለካከት ሳይንሳዊ አስተሳሰብ፣ ኅላዌ-ፈጣሪ (creation) ግን ህይማኖታዊ አስተሳሰብ ብቻ ነውን?1

አያሌ ታላላቅ ሳይንቲስቶች ምንም እንኳ በህይወት ዘመናቸው በዝግመተ-ለውጥ ትምህርት እና አመለካከት ውስጥ ቢያልፉም በዚህ አመለካከት ተፅእኖ ውስጥ ሳይገቡ ዓለም በፈጣሪ እንደተፈጠረች ያምኑ እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል፡፡ እንዲያውም የዘመናዊው ሳይንስ በርካታ ዘርፎች መሠረታቸው በፈጣሪ /እግዚአብሔር/- መኖር የሚያምኑ ሊቃውንት ነበሩ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ምሣሌዎች ለዚህ ጥሩ ማስረጃ ሊሆኑን ይችላሉ፡፡

  • የፊዚክስ ሊቃውንት - ኒውተን፣ ፋራዴይ፣ ማክስዌል፣ ካልቪን
  • የኬሚስትሪ ሊቃውንት - ቦይል፣ ዳልተን፣ ራምሴ
  • የሥነህይወት /ባዮሎጂ/ ሊቃውንት - ሊኒየስ፣ ሜንደል፣ ፓስተር፣ ቨርቾው፣ ሬይ
  • የሥነምድር /ጂኦሎጂ/ ሊቃውንት - ስቴኖ፣ ዉድዋርድ፣ ብሬውስተር፣ በክላንድ፣ ኩቪዬ
  • የሒሳብ ሊቃውንት - ፓስካል፣ ሌብኒትዝ፣ ዩለር

ዛሬም ቢሆን መለኮታዊ አመለካከትን የሚያራምዱ በርካታ ሳይንቲስቶች ከመኖራቸውም በላይ ይኸው አመለካከት በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ብቻ ቁጥራቸው ከ10000 የሚልቁ ሳይንቲስቶች በመጽሐፍ ቅዱስ የፍጥረት አፈጣጠር ዘገባ ይስማማሉ፡፡ ቢሆንም ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የኅላዌ-ፈጣሪ ድርጅቶች አባላት አይደሉም፡፡

በ1993 እ.ኤ.አ በደቡብ ኮርያ በተደረገ ጥናት በአገሪቱ ያለው የኮሪያ ኅላዌ-ፈጣሪ የምርምር ማኅበር 1000 አባላት እንደነበሩት ታውቋል፡፡ በማኅበሩ ከታቀፉት አባላት ውስጥ 100 ሙሉ ፕሮፌሰሮች እና በአብዛኛው ቢያንስ በአንድ የሳይንስ ዘርፍ የማስትሬት እና የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሳይንቲስቶች ይገኛሉ፡፡

የሞስኮ ኅላዌ-ፈጣሪ ሳይንስ ሕብረት በቅርቡ በ10 አባላት ተመስርቶ ከአንድ ዓመት በኋላ የአባላቱ ቁጥር ወደ 120 ሳይንቲስቶች አድጓል፡፡

እነዚህ ሁሉ ታዋቂ ሳይንቲስቶች በዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ውስጥ ቢያልፉም እንኳን አልተቀበሉትም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የእውቀት ማነስ ነው ማለት አያስደፍርም፡። በሌላ በኩል ደግሞ የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት የሳይንቲስቶች ብቸኛ አማራጭ አለመሆኑን ልብ እንድንል ያሳስበናል፡፡ ባለፉት ዘመናት አንዳንድ ሳይንቲስቶች አሠራራቸውን በሳቱ የሀይማኖት መሪዎች ጫና መለኮታዊ አመለካከትን በቅጡ ሳይገባቸው በግድ እንደተከተሉ ሁሉ ዛሬም የዝግመተ-ለውጥን አመለካከት የግድ እንድንቀበል በተቀናበሩ ልዩ ልዩ ተጽዕኖዎች ቀንበር ሥር ልንወድቅ አይገባም፡፡ «ነገር ከሥሩ … » እንደሚባል ግራና ቀኙን በሚገባ ማመዛዘን መልካም ነው፡፡ የአያሌ ዘመነኛ ሊቃውንት ይህንን አስተሳሰብ ማራመድ ንድፈሃሳቡን ትክክለኛ አያሰኘውም፡፡ የዚህች መጽሐፍ ዋነኛ አላማም ብዙ ጊዜ የማንሰማቸውን የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ደካማ ጎኖች እና ስህተቶች ለአንባቢያን አሳይቶ ለውሳኔ የሚረዳ ሃሳብ ማቅረብ ነው፡

የሳይንስ ትርጉምና የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ተቃርኖ

እውነተኛ ሳይንስ አንድን ነገር በመለካት ወይም በማየት ላይ እንዲሁም እንደገና በመሞከርና በማረጋገጥ ሳይ የተመሠረተ ነው፡፡

ለምሳሌ የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ከብዙ ሚሊዮን ዓመታት በፊት ተሳቢ እንሰሳት ወደ አዕዋፋት እንደተለወጡ ቢያስተምርም ይህ መላምት በዓይን የታየና የተረጋገጠ ባለመሆኑ በሳይንሳዊ መለኪያዎች ራሱ የተረጋገጠ ሀቅ አይደለም፡- ሌላው ቀርቶ ዛሬ አንድ ሰው ተሳቢ እንሰሳትን ወደ አዕዋፋት መቀየር ቢችል እንኳን ይህ ሂደት ከብዙ ሚሊዮን ዓመታት በፊት ተካሂዶ እንደነበረ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እግዚአብሔር /ፈጣሪ/ የአፈጣጠር ሂደቱን ዳግመኛ እንዲያሳየን መጠበቅም አግባብ አይደለም፡፡

ሁለቱም አመለካከቶች በእምነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው ማለት ነው፡፡ ለዚህም የሚያቀርቧቸው ጭብጦች እና የመከራከሪያ ነጥቦች አሉ፡፡ በዚሁ አንፃር የኅላዌ-ፈጣሪ አመለካከት አራማጆች ብዙ ተጨባጭ እና አሳማኝ መረጃዎችና ሎጂኮች እንዳሏቸው ያወሳሉ፡፡

ኅላዌ-ፈጣሪያን ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ አላቸውን?

በፍፁም! አሁንም በኅላዌ-ፈጣሪያን ያልተመለሱ ጥያቄዎችና እንቆቅልሾች ገና አሉ፡፡ ነገር ግን የዝግመተ-ለውጥ አመለካከትም ከዚህ ትችት የነጻ አይደለም፡፡ ምንም እንኳ ከኅላዌ-ፈጣሪ ምርምር ጋር ሲነጻጸር በቀረጥ የተሰበሰበ እጅግ በጣም ብዙ ቢሊዮን ገንዘብ ከዝግመተ-ለውጥ ጋር የተያያዙ እንቆቅልሾችን ለመፍታት ቢመደብም ቅሉ በዚህ አንፃር መፍትሔን ሊያመላክት አልቻለም፡፡

በአንጻሩም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ብቻ ብዙ አዳጋች የሚመስሉ ጥያቄዎች በኅላዌ-ፈጣሪያን የምርምር ሂደቶች ሊመለሱ ችለዋል፡፡ በዚሁም ሂደት በሳይንስ እንደሚደረገው አንዳንድ ኋላቀር የነበሩ የኅላዌ-ፈጣሪያን አመለካከቶች ሊለወጡ እና ሊሻሻሉ ችለዋል፡፡ ስለዚህ የኅላዌ-ፈጣሪን አመለካከት በትናንትና መነጽር መተንተን አይቻልም፡፡

የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ምንም እንኳን የተረጋገጠ እውነት ባይሆንም ሁሉም ነገሮች ያለምንም በላኤ-ፍጡር /መለኮት/ ሚና በራሳቸው የተገኙ እንደሆኑ ያስተምራል፡፡ በሌላ አባባል ጥቃቅን እና የተዘበራረቁ ነገሮች በራሳቸው ግዙፉን ሕዋ አስገኙ ማለት ነው፡፡ የዝግመተ-ለውጥ ውስብስብ ሂደት እንዴት እንደተከናወነ ብዙ መሳምቶች ቢሰነዘሩና ቢወድቁም ቅሉ ዝግመተ-ለውጥ /በምንም መንገድ ይሁን/ መካሄዱን ብዙዎች በግትርነት ተቀብለውታል፡፡

አብዛኞቹ ዝግመተ-ለውጠኞች በፍጥረታት አዝጋሚ ለውጥ ሂደት ውስጥ «ፈጣሪ» እንደማያገባው ይስማማሉ፡ ጥቂቶች ዝግመተ-ለውጠኞች ግን በ«ፈጣሪ» መኖር ያምናሉ፡፡ እነዚህ በፈጣሪ መኖር የሚያምኑ ቡድኖች መለኮታዊ ዝግመተ-ለውጠኞች (theistic evolutionists) ተብለው ይጠራሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብላጫዎቹ የፍጥረታት አዝጋሚ ለውጥ ፍጹም ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ እንደተከናወነ ይስማማሉ፡፡

የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ያስከተላቸው ተጽዕኖዎች

1. ይህ አመለካከት ፈጣሪ የለም የሚል አስተሳሰብን ያራምዳጳል፡፡

ማንኛውም «ፈጣሪ የለም» የሚል ግለሰብ ተፈጥሮ ፈጣሪ እንደሌላት ለማስረዳት የዝግመተ-ለውጥ አመለካከትን ይንተራሳል፡፡ በመሆኑም የዝግመተ-ለውጥ ንድፈሃሳብ ለብዙ ኢ-ፈጣሪያዊ አመለካከቶች፣ የህይወት ፍልስፍናዎች እና መዘዞቻቸው መፈብረክ ምክንያት ሆኗሷል፡፡ የእነዚህ አስተሳሰቦች መሠረታዊ ፍልስፍና እና የህይወት መርሆ ደግሞ «በማንም እስካልተፈጠርን ድረስ የማንም ንብረት አይደለንም፡፡ ስለዚህ ለእኛ ከራሳችን በቀር ማንም የህይወትን መርሆች ሊያበጅልን አይችልም» የሚል ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ብዙዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈሩትን የህይወት መርሆች እንደ ተረት ወይም አፈታሪክ ከመቁጠራቸው የተነሣ በእነዚህ «ተረቶች» የሚታሰሩበት ምንም ምክንያት እንደሌለ ይናገራሉ፡፡

2. የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ኢ-ክርስቲያናዊ ነው፡፡

ክርስቲያኖች ከፈጣሪያቸው እንደተሰጣቸው በሚያምኑት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተቀመጠው እግዚአብሔር በመጀመሪያ ትግል፣ ሞት፣ ጭካኔ፣ እልቂት የሌለበት መልካም ዓለም ፈጠረ፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያው ሰው በፈጣሪው ላይ ባደረገው የአመፅ ኅጢአት ምክንያት ጠቅላላ ዓለም ተረገመች፡፡ ይሁንና ይህ ስቃይና ሞት ዘላለማዊ ስላልሆነ ወደቀድሞው ሰላማዊና መልካም ሁኔታ መመለስ የሜቻልበት የተሃድሶ መንገድ እግዚአብሔር አስቀምጣል፡፡ ስለዚህ የሰው ግስጋሴው ዓለም ቀድሞ ስትፈጠር እንደነበረው ዓይነት ወደ ኃጢአት-አልባ እና ሞት-አልባ ሥርዓት ነው፡፡ ሥጋ ለብሶ ወደ ምድር የመጣው ፈጣሪ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ /ሁለተኛው አዳም/ ሰውን ከኃጢአቱና ይህም ካስከተለበት መዘዝ ለማዳን እና መላውን ዓለም ከእርግማን ለመዋጀት ንጹህ ደሙን በመስቀል ላይ በመሞት አፍስሷል፡፡ የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት እውነት ቢሆን ኖሮ ይህ የምስራች ዜና ትርጉም የለሽ እና ፍሬ አልባ በሆነ ነበር፡፡

ይህ ሰውን ከፈጣሪው ጋር ቀድሞ ወደነበረው ግንኙነት መመለስ መቻል የሚያበስር የኢየሱስ ክርስቶስ የምስራች ዜና ያስፈለገበት ምክንያት ከዘመናት በፊት የዘር ምንጫችን /ancestor/ አዳም በኃጢአቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ኅብረት በኃጢአቱ የተነሳ በመቋረጡ ምክንያት ነው፡፡

በጥቅሉ ክርስቲያናዊ የኅላዌ-ፍጡር አመለካከት ከላይ የተጠቀሰውን ሃሳብ ሲያራምድ የዝግመተ-ለውጥ አስተሳሰብ ግን ለሰው ዘር መገኘት ምክንያቱ በቅድመ-ሰው ፍጥረታት መካከል በነበረ የኑሮ ትግል ሀይለኞች ደካሞችን ከውድድሩ በማስወጣት ለረዥም ጊዜ ያካሄዱት ሂደት እንደሆነ ያምናሉ፡፡

 14575-death-creation
 14575-death-evolution
የኅላዊ-ፈጣሪያን እና የዝግመተ-ለውጠኞች የአመለካከት ተቃርኖ

የዘፍጥረት መጽሐፍ የፍጥረታት አፈጣጠር ዘገባ

በመጽሐፍ ቅዱስ የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ከምዕራፍ 1] እስከ 11 በግልጽ እንዳስቀመጠው ፍጥረታት ሁሉ በስድስት መደበኛ ቀናት /ልክ ዛሬ እንደምናውቃቸው ቀናት ዓይነት/ እንደተፈጠሩ እና ዓለምን ሁሉ ያጥለቀለቀ የጥፋት ውሃ ተከስቶ እንደነበረ ያስተምረናል፡፡

ነገር ግን የስድስቱን ቀናት ትርጉም ከዚህ በተለየ ዕይታ የሚያዩ ሰዎች የአስተሳሰባቸው ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም፡- እንዲያውም አላማቸው መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ለቅሬተ-አካሉች ረጅም እድሜ ከሚሰጡ አስተሳሰቦች ጋር እንዲጣጣም ማድረግ ነው፡፡

የኀላዌ-ፈጣሪ አመለካከት እንደሚያስተምረው የሰው ዘር እልቂትና ሞት የተከሰተው ከአዳም መፈጠር በኋላ እንጂ ከአዳም ውልደት በፊት አይደለም፡፡ ይኸው እልቂት የተከሰተው ከአዳም መፈጠር በኋላ ነው ካልን ደግሞ «ህልቁ መሳፍርት ቅሬተ-አካሎችን የያዙት የዓለት ንብርብሮች (፡66፪ ክሃ68) ከየት መጡ?» የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው የኖኅ ዘመን የጥፋት ውሃ እውነት ከሆነ እና በአንድ ወቅት ምድር ሁሉ በዚህ ጎርፍ የተጥለቀለቀች ከሆነች ይህ ሊሆን የማይችልበት ምክንያት የለም፡፡

በመሠረቱ በዓለት ንብርብሮች ውስጥ የሚገኙ ቅሬተ-አካሎች የሚያመለክቱት በፍጥነት መቀበራቸውን እንጂ ብዙዎች እንደሚያምኑት አዝጋሚ ለውጥን አይደለም፡፡ ለምሳሌ በሚገባ የተጠበቁ /ያልፈራረሱ/ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአሣ ቅሬተ-አካሎች ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ ቅሬተ-አካሎች የአሣውን ቅርፍ (scale)፣ ክንፈ-አሳ (fin) የመሳሰሉ ክፍሎች የያዙ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ አንድ አሳ እንደሞተ ወዲያውኑ አፈራራሾች (decomposers) እና በክት-አንሳዎች (scavengers) ይቀራመቱታል፡፡ ስለዚህ አንድ አሳ እንደሞተ በፍጥነት ካልተቀበረና ዝቅጤው (sediment) /ለምሳሌ ጭቃና አሸዋ/ በፍጥነት ካልጠነከረ እንዲህ ዓይነቶች የአሣው የሰውነት ክፍሎች ሳይፈርሱ መቆየት አይችሉም።

14520-ichthyosaur
አንዲት ጥንታዊ የባህር ተሳቢ በወሊድ ላይ እያለች መሞቷን ያሳያል፡፡ ይህች እንሰሳ በአደጋው ምክንያት በፍጥነት የተቀበረች ባትሆን ኖሮ ቅሬተ አካሉ ሳይፈርስ ለሚሊዮን ዓመታት ያሀል በሚገባ ተጠብቆ ለመቆየት አዳጋች ይሆንበታል፡፡
nps.gov14520-fishes
ይህ አሳ ምግቡን እንኳን ሳይጨርስ በድንገት የተቀበረ ነው፡፡

የድንጋይ ከሰል (coal) በረግረጎች ውስጥ በአዝጋሚ ሂደት ሊፈጠር አይችልምን?

በዝግመተ-ለውጠኞች አመለካከት የድንጋይ ከሰል አፈጣጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አመታትን ሊወስድ እንደሚችል ይታመናል።፡ ነገር ግን ደኖች ተነቅለው ከተከማቹ በኋላ በፍጥነት የሚቀበሩበት አጋጣሚ ቢከሰት የድንጋይ ከሰል በፍጥነት ሊፈጠር እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአውስትራሊያ በሚገኝ ያሉርን ተብሎ በሚታወቅ ሥፍራ በአሁኑ ጊዜ በረግረጋማ ሥፍራ የማይበቅሉ ዓይነት የቴምር ዛፍ አያሌ ጉርድራጅ ቅሪቶች በግዙፍ ቡናማ የከሰል መደቦች ውስጥ ይገኛሉ፡፡

በአሜሪካ በሚገኘው የአርጎን ብሔራዊ ቤተሙከራ የሚገኙ ተመራማሪዎች ባደረጉት ሙከራ የእንጨት ቁርጥራጮችን አሲድ ከገባበት ቨክሳ አፈርና ውሃ ጋር በመደባለቅ በአዛሂት (quartz) በተሠራ አየር የማያስገባ ቱቦ ውስጥ በማስቀመጥ እና የአየሩ ግፊት በማይጨምርበት ሁኔታ ለ28 ቀናት በ150°ሴ በማሞቅ ከፍተኛ ጥራት ያለው ጥቁር የድንጋይ ከሰል ሊያመርቱ ችለዋል፡፡ ስለዚህ የድንጋይ ከሰል አፈጣጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታትን የሚፈጅ ሂደት ነው ብሎ መደምደም አይቻልም።

ሰር ኤጅዎርዝ ዴቪድ የተባሉ ታዋቂ አዉስትራሊያዊ የሥነምድር ሊቅ በ1917 ዓ.ም እ.ኤ.አ. በኒኳውካስል አውስትራሊያ ቀጥ ብለው ቆመው ወደ ድንጋይ ከሰልነት በመቀየር ላይ ያሉ የዛፍ ግንዶችን አግኝተዋል፡፡ እነዚህ ግንዶች የታችኛው ጫፋቸው በአንድ የድንጋይ ከሰል መስመር ሲገኝ ሌላው ጫፍ ደግሞ የተለየዩ ንብብራቶችን በማለፍ ከፍ ብሎ ከሚገኝ ሌላ የድንጋይ ከሰል መስመር ውስጥ ይገኛል፡፡ ሁለቱ የድንጋይ ከሰል መስመሮች በዝግመተ-ለውጥ የተራራቀ እድሜ አላቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ የግንድ ጫፎች በአንድ ዛፍ ላይ ቢገኙም በተለያዩ የድንጋይ ከሰል መስመሮች ላይ ስለሚገኙ የተራራቀ አንፃራዊ እድሜ ሊያሰጣቸው ይችላል፡፡

ታዲያ ይህ የዛፍ ግንድ ሁለት በዘመናት የተራራቁ ተብለው በሚታመኑ መስመሮች ውስጥ መገኘቱ አዝጋሚ ለውጥ ተካሄደ ለማለት ያስችላልን? የብዙዎችን አዕምሮ የገዛው የዝግመተ-ለውጥ አስተሳሰብ ዝንባሌ ትክክለኛውን የድንጋይ ከሰል አፈጣጠር ሂደት እንዳይታወቅ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡፡- ይህም ትክክለኛ መንገድ የእጽዋት በጎርፍ መቅሰፍት ተመትተው በፍጥነት መቀበር ነው፡፡

መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ውሃ ታላቅ ሥነ መሬታዊ ለውጥን በሚሊዮን በሚቆጠሩ ዓመታት ሳይሆን በፍጥነት ሊያመጣ ይችላል፡፡

Steve Austin14575-canyon
ስዕል 3
Steve Austin14520-mt-st-helens-layers
ስዕል 4

በስዕል 3 ላይ እንደሚታየው ከሰባት ሜትር የሚልቅ የንብርብር አለት (sedimentary rock) ንጣፍ በአንድ ተሲያት ብቻ ሊፈጠር ችሷል፡፡ ይህም የተከሰተው በአሜሪካ አገር በሚገኝ በዋሽንግተን ግዛት በሴንት ሄለንስ ተራራ ላይ በ1980 ዓ.ም እ.ኤ.አ. በደረሰ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ነው፡፡ ከዚያ በመለጠቅ በተከሰቱ ተከታታይ ፍንዳታዎች የተነሣ የመሬት መንሸራተት፣ የጭቃ ጎርፍ እና ሌሎች ሁኔታዎች የተከሰቱ ሲሆን በአጠ ቃላይ ከመጀመሪያው ፍንዳታ ጀምሮ 180 ሜትር የሚሆን የደለሌ አለት ንብብሮሽ ሊፈጠር ችሷል፡፡

በተጨማሪም በአንድ የጭቃ ጎርፍ ሳቢያ 30 ሜትር የጠለቀ ጭልጤ ሸለቆ (canyon) በአንድ ቀን ብቻ ሊፈጠር ችሏል /ስዕል 4ን ይመልከቱ/፡፡ አንዳንድ በሚሊዮን ዓመታት እድሜ የሚያምኑ ባለሙያዎች ይህንን ክስተት በመመርኮዝ ታላቁ ጭልጤ - ሸለቆ (the Grand Canyon) በተመሳሳይ መንገድ ከደረሰ የጎርፍ መቅሰፍት የተነሳ እንደተፈጠረ ይናገራሉ፡፡ ይህም ለታላቁ ጭልጤ ሸለቆ መፈጠር እንደምክንያት የሚቆጠረውን ሚሊዮን ዓመታትን የፈጀ «የኮሎራዶ ወንዝ ዝግተኛ የመሸርሸር ኃይል» መላምት የሚቃወም ነው፡፡

ቅሬተ-አካሎች (fossils) የዝግመተ-ለውጥ አመለካከትን ያጠናክራሉን?

የዝግመተ-ለውጥ መላምት /ንድፈሃሳብ/ ትክክል ከሆነ የፍልስፍናው አባት ቻርለስ ዳርዊን እንደተናገረው አያሌ አገናኝ ቅሬተ-አካሎች (link fossils) መገኘት ነበረባቸው፡ ለምሳሌ በረጅም ጊዜ አዝጋሚ ለውጥ የተሳቢዎች የፊት እግር ወደ ወፎች ክንፍ ከተለወጠ በመካከል ባሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታት የነበሩ ከፊል እግር፣ ከፊል ክንፍ፣ ከፊል ቅርፍ እና ከፊል ላባ የመሳሰሉ መካከለኛ አካላት የያዙ መካከለኛ እንሰሳትን ቅሬተ-አካላት ማግኘት የግድ ነው፡፡

ቻርለስ ዳርዊን እንደተናገረው የአነዚህ አገናኝ ቅሬተ-አካሉች አለመገኘት በንድፈሃሳቡ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ አመኔታን ሊያሳጣ ይችላል፡፡ አሁንም ከዳርዊን ዘመን 120 ዓመታት በኋላ በአሜሪካ ከሚገኙት ታላላቅ ቤተ መዘክሮች የአንዱ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ዴቪድ ሩፕ የእነዚህ አገናኝ ቅሬተ-አካላሳት «ችግር» እስካሁን ድረስ እንዳልተፈታና-እንዲያውም ጭራሹኑ የዝግመተ-ለውጥ ሽግግርን የሚያመለክቱት ተምሣሌቶች ከዳርዊን ጊዜ ይልቅ ያነሱ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡

ዶ/ር ኮሊን ፓተርሰን በብሪታንያ የተፈጥሮ ታሪክ ቤተመዘክር ዋና የሥነ ቅርሰ ሕይወት (paleontology) ተመራማሪ ሲሆኑ በሙያቸው የቅሬተ-አካል ባለሙያ (paleontologist) እና በአመለካከታቸው ዝግመተ-ለውጠኛ ናቸው፡፡ እፒህ ሰው የዝግመተ-ለውጥ ሂደትን የሚዳስስ ታዋቂ መጽሐፍ ቢጽፉም ለምን የአገናኝ ፍጥረታትን ምስሎች በመጽሐፋቸው እንዳላካተቱ ተጠ ይቀው ከዚህ የሚከተለውን መልስ ሰጥተዋል፡፡

«መጽሐፌ የአገናኝ ፍጥረታት ምስሎች እንደሚጎድሉት በተሰጠኝ አስተያየት ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ በእርግጥም እንዲህ ዓይነት አገናኝ ቅሬተ-አካልም ይሁን ሕያው ፍጥረት ባውቅ ኖሮ እጠቀምበት ነበር፡፡ «እንዲህ ዓይነት አገናኞችን ሰዓሊ በምናቡ አይቶ ሊስል ይገባል» ተብሎ ለተሰነዘረው አስተያየትም ምናባዊውን ምስል ለማግኘት የሚያስፈልገውን መረጃ ከየት ማግኘት ይቻላል? ይሀንን መረጃ ለመስጠ ት እኔ በበኩሌ ብቁ አይደለሁም፡፡ ይህንን ሥራ ደግሞ ለሰዓሊ ብንሰጠ ው አንባቢዎችን ሊያሳስት የሚችል መረጃ ሊሰጥ ይችላል፡፡ መጽሐፌን የጻፍኩት ከአራት ዓመታት በፊት ነው /ጸሐፊው መጽሐፉን በጻፉ ጊዜ በአገናኝ ፍጥረታት እንደሚያምኑ ተናግረው ነበር/፡ ነገር ግን መጽሐፌን አሁን ብጽፈው ኖሮ የተለየ መልክ ሊኖረው እንደሚችል አስባለሁ፡፡ የዝግመተ-ለውጥን አመለካከት የተቀበልኩት በዳርዊን ተፅዕኖ ሳይሆን ለሥነ ባህርይ (genetics) እውቀቴ እንደሚያስፈልገኝ ስላመንኩበት ነው፡፡ ነገር ግን ዝነኛው የቅሬተ-አካል ባለሙያ ስቴፈን ጄ ጉልድ እና ሌሎች የአሜሪካ ቤተ መዘክር (museum) ሊቃውንት አገናኝ ቅሬተአካል እስካሁን ድረስ እንዳልተገኘ ቢናገሩም እነርሱን ለመቃወም ይከብደኛል፡፡ እንደ ሥነቅርሰሕይወት ባለሙያተኛነቴ በቅሬተ-አካል መዛግብት ውስጥ ዘር ግንድን ለመፈለግ በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ብዙ. ጊዜዬን አጠፋለሁ በተጨማሪም እያንዳንዱ ዘአካል (organism) የተገኘበትን ዘር ግንድ ቅሬተ-አካላት ፎቶ ማሳየት አለብህ የሚል አስተያየት ተሰጥቶኛል፡፡ ለዚህ ያለኝ መልስ ግን «ይህንን የሚያስረግጥ አንድም ቅሬተ-አካል የለም» የሚል ነው፡፡

ታዲያ ዝግመተ-ለውጠኞች ያላቸው ተጨባጭ መረጃ ምንድነው? የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አገናኞችን ማቅረብ አለበት፡፡ አንዳንድ ዝግመተ-ለውጠኞች በጣት የሚቆጠሩ አገናኝ ቅሬተ-አካሎች እንዳሉ ይናገራሉ፡፡ ሌሎች ታዋቂ ባለሙያዎች ደግሞ ጭራሽ አንድም አገናኝ እንዳለ አያምኑም፡፡

አንዱ «አገናኝ» ተብሎ የሚጠራው በብዛት የማይታወቀው እንግዳ ቅሬተ-አካል ፍጥረት ሪረሜኔምሥፖሃሪ#ዕያዕ ነው /ስዕል 5ን ይመልከቱ/፡፡ ይህ አገናኝ በተሳቢዎችና በወፎች መደብ መካከል የነበረ አገናኝ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህም የሆነው የሁለቱንም ምድቦች ባህርያት ስለሚጋራ ነው፡። ቢሆንም ይህ ቅሬተ-አካል ጥርጣሬን የሚያስወግዱ ወሳኝ የሽግግር አካላት ይዞ አናየውም፡፡ ላባዎቹ ትክክለኛ ላባዎች ክንፎቹም ትክክለኛ ክንፎች ሲሆኑ ልክ እንደ አንዳንድ ወፎች ወደ ኋላ የዞሩ ማጉርጦችና (claw) ጥምዝ እግሮች አሉት፡፡

14520-archaeopteryx
ስዕል 5

ቢሆንም አንዳንዶች እንደሚያስቡት ይህ አገናኝ ቅሬተ-አካል ሯጭ ባለላባ ዳይኖሶር (running feathered dinosaur) አልነበረም፡፡

እንደ 7#፳7# ያሉ አሁንም በምድረ ገጽ የሚገኙ ዝርያዎችም እንዲሁ የተለያዩ የእንሰሳት መደቦችን ባህርያት አጣምረው ይይዛሉ፡፡ ይህ ትንሽ እንግዳ ፍጥረት የአጥቢዎች ዓይነት ፈር (fur)፤ የዳክዬ ዓይነት ምንቃር (beak)፣ የቢቨር2 /ገድቤ አይጤ/ ዓይነት ጭራ፣ እና የእባብ ዓይነት የመርዝ እጢዎች አሉት፡፡ በተጨማሪም እንደ ተሳቢዎች እንቁላል ሲጥል እንደ አጥቢዎች ደግሞ የማጥባት ባህርይ አለው፡፡ ይህም ጥሩ የጣምራ ባህርያት ምሣሌ አድርጎታል፡፡ ቢሆንም ከእነዚህ ከተጠቀሱት የእንሰሳት መደቦች የማናቸውም ሁለቱ አገናኝ አይደለም፡፡

ይህ የአገናኝ ቅሬተ-አካላት አለመገኘት «የሰው አመጣጥ ዝግመተ-ለውጣዊ ነው» በሚለው አስተሳሰብ ውስጥ ክፍተት በመፍጠሩ ሳቢያ ተመሳሳይ ደንቃራ ገጥሞታል። «የሰው ዘር ግንድ ናቸው ተብለው የሚታመኑ ብዙ ቅሬተ-አካሎች አሉ» እየተባለ በየጊዜው ስለሚነገር ይህ ትችት ሊያስገርም ይችላል፡፡ ሁሉንም የዘር ግንድ መላምቶች ዘርዝሮ መወያየት ባይቻልም ባለፈው ክፍለዘመን እንኳን ብዙዎቹ መላምቶች አዲስ እጩ ዘር ግንድ በተገኘ ቁጥር ውድቅ እየተደረጉ በአዲስ መላምት ሲተኩ ቆይተዋል፡፡

አሁን ባለው ስምምነት መሠረት ሉሲ የተባለችው ቅሬተ-አካል የምትመደብበት australopithicines/habilines የሚባለው ሰፊ ቡድን የሰው ዘር ግንድ እንደሆነ ይታመናል /ስፅል 6ን ይመልከቱ/፡፡

ዶ/ር. ቻርለስ ኦክስናርድ ዝግመተ-ለውጠኛ የሥነ-ብልት (anatomy) ምሁር ናቸው፡፡ እፒህ ተመራማሪ ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ ባደረጉት በኮምፒዩተር የታገዘ መጠነ ሰፊ ምርምር ሉሲ የምትገኝበት የቅሬተ-አካል ቡድን የሰው ዘር ግንድ ነው የሚለውን ሃሳብ አይቀበሉትም፡፡

14520-lucy
የሉሲ

እንደ እፒሁ ተመራማሪ አባባል ምንም እንኳ ቀድሞ ይህ የሉሲ /ድንቅነሽ/ ቡድን ሰው መሰል ወይም ቢያንስ የሰው እና የኤፕ3 አገናኝ እንደሆነ ቢታመንም እውነታው ግን ይህ ቡድን ሰው እና የአፍሪካ ኤፕ ከሚያሳዩት ልዩነት የበለጠ ከሁለቱ ቡድኖች የሚለይ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ሉሲ የምትገኝበት የአውስትራሎፒቴሲንስ ቡድን የተለየ ነው፡፡ እንደ ተመራማሪው አባባል ሉሲ የተሰኘችውን ቅሬተ-አካል ካገኙት ሳይንቲስቶች በቀር «ይህ ቡድን የሰው ዘር ግንድ አይደለም» የሚለውን አመለካከት የሚጋሩ ተመራማሪዎች ቁጥር በየጊዜው እያደገ ይገኛል፡፡

ሆሞ ኢሬክተስ የተባሉት ዝርያዎችስ? እነዚህ ዝርያዎች ከኖኅ ዘመን የጥፋት ውሀ በኋላ ይኖሩ የነበሩ ለየት ያለ አጽመ-ዝርያ (bony racial variation) የሚያሳዩ እውነተኛ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ከኖኅ ዘመን የጥፋት ውሃ በኋላ በነበረው በፍጥነት ተለዋዋጭ የአካባቢ ሁኔታ ምክንያት በተከሰተው የምርጦሽ (selection) ሂደት ጫና እና እግዚአብሔር ሰዎችን ቋንቋቸውን ደባልቆ በመበተኑ ምክንያት በተፈጠ ሩት ትናንሽ የተነጣጠሉ ሕዝቦች ምክንያት ፈጣን መገለል (isolation) እና በራሂያዊ (genetic) ልዩነቶች እያደጉ እንዲሄዱ አመቺ ሁኔታዎች ተፈጠ ሩ። ይህ የዝርያ ምጣቄ (racial variation) አጽመ-ጠባዮችንም (bony features) ይጠቀልላል፡፡

በተለያዩ የሰው ዘር ነገዶች (races) መካከል ካለው ሰፊ ልዩነት ጋር ሲነጻጸር በኢሬክተስ እና በሰው አጽም መካከል ያለው ልዩነት ያን ያህል ትልቅ አይደለም፡፡ እንዲያውም ኢሬክተስ ብቻ ሳይሆን በአማካይ ከ«ዘመናዊው ሰው» የሚበልጥ የአንጎል መጠን ያላቸው ኒአንደርታል እና ክሮማግነን የሚባሉት ዝርያዎች አሁን ካለው «ዘመናዊ ሰው» ጋር በአውሮፓ አህጉር በተመሳሳይ ወቅት ይኖሩ እንደነበር ታወቋል፡፡

የራሳቸውን የዝግመተ-ለውጠኞችን የጊዜ ሚዛን እና መመዘኛ ለእንሰሳት ምደባ እንደ መመዘኛ ተጠቅሞ የዘረሰብ (hominid) ቅሬተ-አካላት ግኝቶችን በቻርት ላይ በመደርደር ትክክለኛ ዝግመተ-ለውጣዊ ቅደም ተከተልን (evolutionary sequence) ለማወቅ ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡

በውኑ ዝግመተ-ለውጥ አሁን እየተካሄደ ነውን?

ምንም እንኳ ሕይወት ያላቸው ነገሮች በየጊዜው ለውጥን ቢያካሂዱም ይህ ለውጥ ግን ዝግመተ-ለውጥ ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ የተለያዩ ምግቦችን ማዘጋጀት እንዲቻል የሚረዱ መመሪያዎች (recipes) እንዳሉ ሁሉ እንዲሁ ፍጥረታት ምን ዓይነት ሊሆኑ እንደሚገባቸው የሚወስን ፕሮግራም በውስጣቸው ይገኛል፡፡ ይህ ፕሮግራም ለምሳሌ አንድ ሰው ሊኖረው የሚገባውን የዓይን ቀለም፣ የጸጉር ዓይነት፣ ቁመት እና የመሳሰሉ ባህርያት ይወስናል፡ነ፡ ይህ መረጃ የተጻፈው ደግሞ ዲ.ኤን.ኤ (dna)4 በሚባል ረጅም ሞሌኪውል ላይ ነው፡፡

14575-dna-information
ስዕል 7

የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት እንደሚያስተምረው ከአንድ ሕዋስ ብቻ የተሠራ (unicellular) እንደ አሜባ ያለ ኢምንት በአጉሊ መነፅር (microscope) ብቻ የሚታይ ፍጥረት በረጅም ጊዜ የዝግመተ-ለውጥ ሂደት ፈረስን ወደመሰለ ውስብስብ እና ብዘ-ሕዋሳዊ (multicellular) ትልቅ ፍጥረት ሊለወጥ ችሏል ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን አንድ-ሕዋሳዊ የሆኑ ጥቃቅን ፍጥረታትም ቢሆኑ በውስጣቸው ውስብስብ እንደሆኑ ባይካድም ነገር ግን ፈረስን እንደመሳሰሉ ትላልቅ ፍጥረታት የሚያክል ብዙ መረጃ ውስጣቸው የለምፎ፡፡ ማለትም በፈረስ ውስጥ የሚገኙ ዓይንን፣ ጆሮን፣ ደምን፣ አንጎልን፣ ጡንቻን፣ ወዘተ የሚሠሩ መረጃዎችና መመሪያዎች በውስጣቸው የላቸውም፡፡

ስለዚህ በስዕል 7 እንደተመለከተው በዝግመተ-ለውጥ ሂደት ከ «ሀ» ወደ «ለ» ለመለወጥ እያንዳንዳቸው የመረጃ ይዘትን የሚጨምሩ ብዙ ደረጃዎችን ማለፍ ይጠይቃል፡፡ እነዚህ አዳዲስ የመረጃ ጭማሪዎች ደግሞ አዳዲስ የቅርጽ (structural) እና የግብር (functinal) ለውጦችን በማምጣት በእያንዳንዱ የዝግመተ-ለውጥ ደረጃ ውስብስብነትን መጨመር ይጠ በቅባቸዋል፡፡

ይህን የመረጃ ለውጥ/እድገት በመጠኑም ቢሆን ማየት ቢቻል ኖሮ ለምሳሌ አንድ አሣ በረጅም ጊዜ ዝግመተ-ለውጥ ወደ ፈላስፋ ሰው ሊለወጥ ይችላል የሚለውን ክርክር ከቶውንም መካድ ባልተቻለ ነበር፡፡

ቀደም ብለን እንዳየነው ምንም እንኳ አያሌ ጥቃቅን ለውጦች ሕይወት ባላቸው ነገሮች ሳይ ቢኖሩም እነዚህ ለውጦች ግን የመረጃ ጭማሪን የሚያመጡ አይደሉም፡፡ እንዲያውም ዝግመተ-ለውጠኞች እነዚህን ጥቃቅን ለውጦች ቀጥሎ እንደምናየው ለራሳቸው እንደ ማስረጃ አድርገው ሊጠ ቀሙባቸው ይሞክራሉ፡፡

ተፈጥሯዊ ምርጦሽ (natural selection) እና ዝግመተ-ለውጥ አንድ አይደሉም!

ቀደም ሲል እንዳየነው ሕይወት ያላቸው ነገሮች በውስጣቸው የሚገኘውን ይህን መረጃ በማስተላለፍ ራሳቸውን ያራባሉ፡፡ የሰውን ዘር እንደምሣሌ ብንወስድ የወንዱ ዲ.ኤን.ኤ (DNA) በወንዴ ዘር (sperm) በኩል ሲተላለፍ የሴቷ ደግሞ በእንቁላል በኩል ይተላለፋል፡፡ በዚህ መንገድ መረጃ ከአባት እና ከእናት ወደሚቀጥለው ትውልድ ይሸጋገራል፡፡

ሁላችንም በሕዋሶቻችን ውስጥ ሁለት ረጃጅም ትይዩ ገመድ መሰል መረጃዎች አሉን፡ እነዚህም አንዱ ከአባት ሌላው ደግሞ ከእናት የወረስናቸው ናቸው፡፡ በሕዋሶች ውስጥ በሚገኙ ረቂቅ ቴክኖሎጂዎች አማካይነት በዲ.ኤን.ኤ ላይ ያለው መረጃ ይነበባል፡፡ ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ተመሳሳይነታቸው ፍጹም የማይሆንበት ምክንያት መረጃዎች በተለያየ መንገድ ስለሚቀላቀሉ ነው፡፡ ይህ የመረጃ ብወዛ በሰዎች፣ በእንሰሳት ወይም በእጽዋት ውስጥ ሰፊ ምጣቂቁን (variation) ያመጣል፡፡

ለምሳሌ ከአንድ ጥንድ የተወለዱ ውሾችን ሁሉንም በአንድ ክፍል አስቀምጠን ብናስተያያቸው ከቁመታቸው ጀምሮ ሌሉችን ልዩነቶች ማየት እንችላለን፡፡ ነገር ግን ይህ የምጣቄ- ሂደት አዳዲስ የመረጃ ለውጦችን አላስከተለም፡፡ ምክንያቱም በወለዶች (offspring) ውስጥ ያለው መረጃ ቀድሞውንም በወላጆች ውስጥ የነበረ ነውና፡፡

ስለዚህ አንድ አራቢ አጫጭር ወለዶችን መርጦ ቢያራባቸው እንደገናም ከአዲሶቹ ትውልዶች ውስጥ እንዲሁ አጫጭሮቹን መርጦ ለተከታታይ ትውልዶች ማራባቱን ቢቀጥል በመጨረሻ የአጭር ርቢ (breed) ቢፈጠር አያስደንቅም። ነገር ግን ምንም አዲስ መረጃ በዚህ ሂደት ውስጥ እንዳልተፈጠረ ያስተውሉ፡፡ በአጭሩ አራቢው ያደረገው ነገር ቢኖር በእርሱ አመለካከት ወደሚቀጥለው ትውልድ በራሂዎችን (genes) ለማስተላለፍ ብቁ ናቸው ያላቸውን ውሾች መርጦ ማዳቀል ነው፡፡ በዚሁም ሂደት ሌሎቹን ውሾች ትቶአቸዋል ማለት ነው፡፡

በእርግጥ አንድ አራቢ /ረጅም እና አጭር ባህርይ ቀላቅሎ ከያዘ ርቢ ይልቅ/ አጫጭር ርቢዎችን ብቻ መርጦ ቢያራባ ምንም እንኳ ማራባቱ እና ምርጦሹ እስከፈለገ ጊዜ ድረስ ቢቀጥል ረጅም ዓይነተኛ ዘር የመወለድ እድል የለውም፡፡ ምክንያቱም የረጅም ቁመት መረጃ ከዚያ ሕዝብ ውስጥ በምርጦሹ ሂደት ጠፍቷል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጥሮ አንዳንዶችን መርጣ ሌሎችን መተው ትችላለች። በዚህም መሠረት የተመረጡት መረጃዎቻቸውን ወደሚቀጥለው ትውልድ በማስተላለፍ ዝርያቸውን የመቀጠል እድላቸው ከተተውት ይልቅ እጅግ ይበልጣል፡፡ ተፈጥሯዊ ምርጦሽ ከሌሉቹ ይልቅ ለአንዳንድ መረጃዎች በማድላት የተወሰኑ መረጃዎች ከሕዝቡ ውስጥ እንዲጠፉ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ነገር ግን ይሀ ሂደት ምንም ዓይነት አዲስ መረጃን አይፈጥርም፡፡

በዝግመተ-ለውጥ ንድፈሃሳብ መሠረት አዲስ መረጃዎች ሊፈጠሩ የሚችሉት በድንገለውጥ (mutation) ነው፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው መረጃዎች በሚተላለፉ ጊዜ በሚከሰት ነሲባዊ እና ድንገተኛ (random and accidental) ስሕተቶች ነው፡፡ እርግጥ ነው እነዚህ ስህተቶች እንደተከሰቱ እናውቃለን፡፡ መጪው ትውልድም እነዚህኑ እንከናም (defective) መረጃዎች በመቀበል ባህርዩን ሊወርስ እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡ ይህ እንከን ወደ መጪ ትውልዶች በመተላለፍ ላይ እያለ በተጨማሪ ሌሳ የድንገለውጥ እንከን በዚያው የትውልድ መስመር ላይ ቢከሰት ደግሞ የድንገለውጥ እንከኖች በዚያ የትውልድ መስመር ላይ መከማቸት ይጀምራሉ፡፡ ይህም የድንገለውጥ እንከኖች ማሻቀብ (mutational load) ወይም በራሂያዊ ጭነት (genetic burden) ይባላል፡፡

በሰው ዘር ውስጥ ተወራራሽ በሽታዎችን በማምጣታቸው ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ እንደዚሀ ዓይነት በራሂያዊ እንከኖች ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ ተወራራሽ በሽታዎች ለምሳሌ ማጭዴ ህዋስ ሰሀደም (sickle cell anemia) እና መፍቀሬ ድማትን (hemophilia) ያጠቃልላሉ፡፡

ጠቃሚ ድንገለውጦች አሉን?

ዝግመተ-ለውጠኞች ድንገለውጦች እጅግ በጣም ጎጂ አለበለዚያም ትርጉም የለሽ በራሂያዊ ሁከቶች እንደሆኑ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን አመለካከታቸው ተቀባይነትን ያገኝ ዘንድ ጠቃሚ ድንገለውጦች አልፎ አልፎም ቢሆን መከሰት እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በእርግጥ ህይወት ያላቸው ነገሮች በአንድ አካባቢ ለመኖር እና ዝርያን ለመቀጠል እንዲችሉ የረዷቸው አንዳንድ በጣት የሚቆጠሩ ድንገለውጦች አሉ፡፡ ለዚህም ከዚህ የሚከተሉትን ምሣሌዎች ማየት ይቻላል።

በዋሻ ውስጥ የሚኖሩ ዓይን አልባ አሣዎች በዓይን በሽታ ስለማይጠቁ የተሻለ ህይወትን ይመራሉ፡፡ ይህ ዓይን አልባነት በድንገለውጥ የመጣ እንከን ቢሆንም እንደተመለከትነው በዚህ አንፃር ለአሣዎቹ ጠቅሟቸዋል፡፡

ነፋሻማ በሆነ ባህር ውስጥ በዓለቶች ላይ የሚኖሩ ክንፍ-አልባ ጥንዚዛዎች በንፋስ የመወሰድ ወይም የመስጠም አደጋ ስለማይደርስባቸው የተሻለ ህይወትን ይመራሉሌ፡፡

በሌላ አቅጣጫ ግን የዓይን መጉደል ወይም ክንፍን ለመሥራት የሚያስችለው መረጃ መጉደል ምንም እንኳ ለእነዚህ እንሰሳት በተለይ ቢጠቅማቸውም በፊት በአግባቡ ይሠራ የነበረ ብልት እንከን እንደገጠመው ያሳያል፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ ድንገለውጦች ምንም እንኳ ከእንስሶቹ መሰንበት (survival) አንፃር ጠቃሚ መስለው ቢታዩም ቅሉ አንድ የሚጭሩት ጥያቄ አለ፡፡

ይኸውም እነዚህ ድንገለውጦች ጠቃሚ ቅርጸ-አካሉሎችን ወይም ጠቃሚ ተግባራትን ለማምጣት የሚችሉ እውነተኛ እና አሻቃቢ የመረጃ ጭማሪዎችን ያሳያሉ ወይ? የሚል ነው፡፡ በሶስት አፅቄዎች (insects) ውስጥ የሚታየው ፀዘረ-ሶስት አፅቄ ኬሚካል (insecticide) የመቋቋም ኃይል ለዚህ ጥያቄ በቂ መልስ ሊሆን አይችልም፡ ምክንያቱም ሶስት አፅቄዎች ፀረ– ተባዩን መቋቋም እንዲችሉ የሚያደርጋቸው መረጃ አስቀድሞም ቢሆን በጥቂት አባላት ውስጥ ነበር እንጂ አዲስ የተፈጠረ መረጃ አይደለምና ነው፡፡

በመሠረቱ ፀረ-ሶስት አፅቄ ኬሚካል ርጭትን ተከትሎ ትብ (sensitive) ትንኞች በዲዲቲ ከተገደሉ በኋላ ቀሪዎቹ በሚራቡበት ጊዜ በሟቾቹ ብዙኃን ውስጥ የነበሩ አንዳንድ መረጃዎች በዚያው ስለሚጠፉ በተረፉት አናሳዎች ውስጥ እነዚህ መረጃዎች ለዘላለሙ አይገኙም፡፡

ህይወት ባላቸው ነገሮች ውስጥ የሚከሰቱ ውርስ ለውጦችን በምንመለከትበት ጊዜ ሁለት ሁኔታዎችን እናያለን፡፡ ወይ መረጃ መጠኑ ሳይለወጥ እንዳለ ይቆያል /ምንም እንኳን በተለያየ መንገድ ብወዛ ቢካሄድም/ አለበለዚያ ደግሞ በድንገለውጥ ወይም በውድመት (extinction) ሳቢያ ይቀንሳል፡፡ ሆኖም በመረጃ አሻቃቢ የሆነ የዝግመተ-ለውጥ አካሄድ በጭራሽ አናይም፡፡

በመሠረቱ መራባት ማለት የመረጃ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ ማለት ነው፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው በዚህ የመራባት ሂደት የሚተላለፈው የመረጃ መጠን ወይ እንዳለ ይቆያል አለበለዚያም እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ በአንጻሩም የእንከናም በራሂዎች ሁከት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ህይወት ባላቸውም ሆነ በሌላቸው ነገሮች ውስጥ እውነተኛ እና አሻቃቢ የሆነ መረጃን ያካተተ ዝግመተ-ለውጥ አይታይም፡፡

በአጠቃላይ በዓለም ላይ የሚገኙ ህይወት ያላቸው ነገሮችን በሙሉ ብንመለከት ትውልዱ እየቀጠለ ሲሄድ የሚተላለፈው የመረጃ መጠን እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ በዚህ መሠረት በጊዜና በትውልድ አቆጣጠር ወደ ኋሳ ብንሄድ የመረጃው ክምችት እየጨመረ መሄድ አለበት ማለት ነው፡፡

ነገር ግን በጊዜ ቀመር ወደ ኋላ ስንጓዝ ወይም መረጃ እየተከማቸ ሲሄድ «ወሰን አልባ ውስብስብ ፍጥረታት ከወሰን አልባ ጊዜ በፊት ይኖሩ ነበር» (infinitely complex organisms used to live an infinte time ago) ብሎ መደምደም ስለማይቻል ወደ ኋላ የምናደርገው ጉዞ ግዴታ የዚህ ውስብስብ መረጃ መነሻ /መጀመሪያ/ ላይ ያቆማል፡፡ ቢሆንም የሳይንስ መርሆች እንደሚጠቁሙት /እንደሚያምኑበት/ አንድ ቁስ አካል በራሱ ይህን መሰል ውስብስብ መረጃ ከየትም ሊያመጣ አይችልም፡፡ ስለዚህ ብቸኛው አማራጭ በአንድ ወቅት ከዚሀ የዓለም መዋቅር ውጪ የሆነ አንድ የፈጣሪ አዕምሮ በቁስ አካሉ ላይ እውቀትን /መረጃን/ በመክተት የመጀመሪያ ዓይነት እንሰሳትን እና እጽዋትን ፈጥሯል ማለት ነው፡፡

በፍጥረት ሕግ መረጃን ከምንም መፍጠር ስለማይቻል በአሁኑ ዘመን በሚገኙ ህይወት ያላቸው ነገሮች የዘር ግንዶች ላይ የተደረገው የመረጃ ሙሌት በተዓምራት ወይንም በሌላ ቋንቋ በበሳኤ-ተፈጥሯዊ (supernatural) ሂደት የተከናወነ ነው ማለት ነው፡፡

ይህም አስተሳሰብ በመጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት መጽሐፍ ሳይ ፍጥረታትን «እንደ ወገኑ ፈጠረ…ብዙ ተባዙ ብሎም ባረካቸው» ተብሎ ከተጻፈው ዓረፍተ ነገር ጋር ይጣጣማል፡፡ ለምሳሌ የውሻን ዘር እናስብ፣ የውሻ ዘር መጀመሪያ ሲፈጠር ብዙ ምጣቄዎችን በውስጡ ይዚዛል፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ ላይ ምንም በራሂያዊ እንከን አልነበረበትም፡፡ ነገር ግን የእነዚህ የመጀመሪያ መረጃዎች ብወዛ (recombination) በረጅም ጊዜ ምርጦሽ እንደ ተኩላ የመሳሰሉ ሌሎች መሰል ዝርያዎችን ሊያመጣ ይችላል፡፡

ተፈጥሯዊ ምርጦሽ ይህንን መረጃ መምረጥ እንጂ አዲስ መረጃ መፍጠር እንደማይችል ስለ ትንኝ ባየነው ምሣሌ ላይ ተገንዝበናል፡፡ ቢሆንም ምንም አዲስ መረጃ ሳይፈጠር በዚህ ሂደት የተገኙ ወለዶች ልዩነታቸው በጣም ሰፍቶ የተለያዩ ዝርያዎች እስኪያሰኛቸው ድረስ ሊሄድ ይችላል፡፡

በዚህ መሠረት አንድ የውሻ ርቢ ስብስብ በሰው ሰራሽ ምርጦሽ ወደተለያዩ ዓይነት ርቢዎች ሊመጥቅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ አጫጭር ውሾች ብቻ መርጠን እያዳቀልን ብንቀጥል ረጃጅም የውሻ ርቢ በረጅም ጊዜ ሂደት ከዚህ የትውልድ ሀረግ ውስጥ ይጠፋል ማለት ነው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የመጀመሪያው የዝሆን ዘር በውስጡ ባለው መረጃ ላይ በተካሄደ ተፈጥሯዊ ምርጦሽ ሰበብ የአፍሪካ ዝሆን፣ የህንድ ዝሆን፣ ማሙዝ (mammoth) እና ማስቶዶን (mastodon) ወደተሰኙ አራት ቡድኖች መጥቆ ሊሆን ይችላል፡፡

ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ለውጥ በመጀመሪያው የዝርያ ዓይነት ውስጥ በነበረው የመረጃ ክምችት መጠን የተገደበ እንደሆነ መታወቅ አለበት፤፤ ስለዚህ ይህ ዓይነቱ ምጣቄ እና የአዲስ ዝርያ መፈጠር (speciation) ለምሳሌ አንድን አሜባ ወደ አሾካዶ ዛፍ ሊቀይረው እንደማይችል በግልጽ መታወቅ አለበት፡፡ አሜባ ወደ አሾካዶ ዛፍ ለመለወጥ የረጅም ጊዜ የመረጃ ማሻቀብ ሂደትን ማለፍ አለበት፡፡ አሁን ያየነው ተፈጥሯዊም ይሁን ሰው ሰራሽ ምርጦሽ ግን ምንም ዓይነት የመረጃ ማሻቀብን (information adding) አያካትትም፡፡ ይህን የበራሂያዊ ምንጭ እየሳሳ መሄድ አንዳንዶች «ዝግመተ-ለውጥ» ብለው ሊጠሩት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ የመረጃ እየሳሳ መሄድ የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ከሚያራምደው «የመረጃ ማሻቀብ» አስተሳሰብ ጋር ፈጽሞ የተቃረነ ነው፡፡

ህይወት ባሳቸው ነገሮች ውስጥ ያሉ ተመሳሳይነቶችስ እንዴት ይታያሉ?

የሁሉም ነገሮች ፈጣሪ አንድ እንደመሆኑ መጠን ለተመሳሳይ ቅርጸ-አካሎች (structures) ወይም ለተመሳሳይ ግብሮች (function) ተመሳሳይ ንድፍ ሊኖር ይችላል፡፡ ሞሌኩላዊ ተመሳሳይነቶች በዚሁ ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ከእንቁራሪት ይልቅ ቺምፓንዚ የሰውን ዘር ይመስላል፡፡ ይህ መመሳሰል በውስጣዊ ስሪቱ እና በፕሮቲኖቹ ቅርጽ ይንጸባረቃል፡፡

ለምሳሌ በስዕል 8 ላይ እንደሚታየው በአንዳንድ ባለአከርካሪ እንሰሳት (vertebrates) የቀዳማይ መሆር (forelimb) አጥንት አቀማመጥ ላይ ያለውን ተመሳሳይነት ዝግመተ-ለውጠኞች ዝምደት (homology) ብለው ይጠሩታል፡፡ ለዚህ ተመሳሳይነት በአጠቃላይ ሁለት የተለያዩ ምክንያቶች ይሰነዘራሌ፡፡ አንደኛው ቡድን የሚሰጠው ምክንያት «የሁሉም እንሰሳት ዘር ግንድ አንድ በመሆኑ ነው» የሚል ሲሆን ሁለተኛው ቡድን ደግሞ «የሁሉም እንሰሳት ፈጣሪ አንድ በመሆኑ ነው» ይላል፡፡ ነዢ ግን ይህ በእንሰሶቹ መካከል ያለ መመሳሰል በማንኛውም ቡድን ቢሆን እንደ ማረጋገጫ ሊቀርብ አይችልም።

14575-forelimbs
ስዕል 8

በዚህ አንጻር ዝግመተ-ለውጠኞች ያጋጠሟቸው ትላልቅ መሰናክሎች አሉ፡፡ በብዙ ፍጥረታት ውስጥ በንጽጽር እንደታየው ዝምድ (homologous) ቅርጸ-አካሎች ወይ ምንም ከማይገናኙ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እና ከባዕድ (non-homologous) በራሂዎች አለበለዚያም ከተለያዩ የጽንስ ዋና ክፍሎች (embryonic segments) ሊመነጩ ስለሚችሉ ይህ ዋና ደንቃራ ሆኖባቸዋል፡፡

በነገራችን ላይ እነዚህ ተመሳሳይ ቀዳማይ መሆር አጥንት ያላቸው እንሰሳት ተመሳሳይ የዳህራይ መሆር (hindlimb) አጥንት እንዳላቸው ልብ ይሏል። ይህ ማለት ደግሞ «እነዚህ ፍጥረታት በመላ አንድ ጥንድ መሆር ከነበራቸው ፍጥረታት አዝጋሚ በሆነ የለውጥ ሂደት የመጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ባለአንድ ጥንድ መሆር እንሰሳት ደግሞ የአሁኖቹ እንሰሳት ቀዳማይ እና ዳህራይ መሆሮች የዘር ግንድ ናቸው» ማለት ነው፡፡

ቢሆንም ብዙ ዝግመተ-ለውጠኞች ይህንን ሃሳብ አይቀበሉትም፡፡ ታዲያ ይህን ተመሳሳይነት በአጭሩ «የፈጣሪ ምርጫ» ብሎ መቀበል አያስኬድምን?

የሞሌኩላዊ ሥነህይወት (biochemistry) ተመራማሪ የሆኑት ማይክል ዴንተን በአመለካከታቸው ኅላዌ-ፈጣሪያዊ አይደሉም። ነገር ግን በተለያዩ ዝርያዎች ፕሮቲኖች መካከል ባደረጉት ህየወ-ኬሚካዊ (biochemical) ንጽጽር የተገኘው ውጤት በስፋት የሚታመንበትን «የጋራ ዘር ግንድ» (common ancestor) ንድፈሃሳብ ከመደገፍ ይልቅ ዝርያዎቹ ፈጽሞ የተለያዩ አይነቶች እንደሆኑ አመላክቷል፡፡

ዝግመተ-ለውጣዊ ቅርሰ-አካሎች
Evolutionary Leftovers (Vestigial Organs)

በሀያኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ዝግመተ-ለውጠኞች «በሰውነታችን ውስጥ ከ80 የሚበልጡ ጥቅም የሌላቸው ቅርሰ-አካሎች (vestigial organs) አሉ» ብለው የተናገሩት በሙሉ እምነት ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ግን የእያንዳንዱ «ቅርሰ-አካል» ጥቅም በጥናትና ምርምር መታወቅ ሲጀምር ግን በአሁኑ ጊዜ «ቅርሰ-አካል» ብለው የሚጠሩት አካል እስከማጣት ድረስ እየደረሱ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ይህ የመከራከሪያ ነጥብ ለዝግመተ-ለውጠ ኞች የተሳካ ሆኖ አልተገኘም፡፡

ለብዙ ጊዜ «ትርፍ» አንጀት ብለን የምንጠራው የአካል ክፍል «ጥቅም የሌለው ቅርሰ-አካል» ተብሎ ለረጅም ዓመታት ቢታመንበትም በአሁኑ ወቅት ግን በልጅነት ጊዜ ልክፈትን (infection) መከላከል እንደሚችል የሚጠቁሙ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ ነው፡፡

14575-embryos
ስዕል 9

ምንም እንኳ ከረጅም ጊዜ በፊት ጆምሮ ትልቅ እክል ቢገጥመውም አልሞት ባይ ተጋዳይ በመሆን የዘለቀው ሌላው አመለካከት ደግሞ «የሰው ጽንስ የሚያልፍባቸው የእድገት ደረጃዎች በዝግመተ-ለውጥ የሰው ዘር ካለፈባቸው የእድገት ደረጃዎች ጋር አንድ ናቸው» (ontogeny recapitulates phylogeny) የሚለው አመለካከት (Theory of recapitulation) ነው፡፡ ይሀም ቢሆን ጭብጥ የሌለው ንድፈሃሳብና የተሳሳተ ድምዳሜ ነው፡፡

የተለያዩ ህንፃዎች፣ ቤቶችና ፋብሪካዎች በሚገነቡ ጊዜ በመጀመሪያ መሠረታቸው ሲታይ ሁሉም አንድ እንደሚመስሉ እና ለመለየት እንደሚያዳግቱ ሁሉ በስዕል 9፡፡

ላይ የምናያቸው የተለያዩ ባለአከርካሪ አጥንት እንሰሳትም በጽንስ (embryo) ደረጃ ሊመሳሰሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ ህንጻው እያደገ ሲሄድ ምን እንደሆነ መለየት እንደሚቻል ሁሉ ፳ንሱም እያደገ ሲሄድ የተለየ ቅርፅን እየያዘ ይሄዳል፡፡

የሰው ዘር ታሪክ

በአሁኑ ጊዜ የሰው ዘር የሕዝብ ቁጥር ያለማቋረጥ በዓመት ከአንድ በመቶ በላይ እንደሚጨምር ይታመናል፡፡ በሽታ፣ ድርቅ፣ ጦርነት እና የመሳሰሉትን ሞት አምጪ አደጋዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የእድገቱን መጠን በዓመት 0.5 በመቶ አድርገን ብናስብ እንኳን በዚህ ፍጥነት በኖኅ ዘመን በነበረው በአራራት ተራራ ከጥፋት የተረፉት ስምንት ሰዎች ወደ አሁኑ የሕዝብ ቁጥር እንዲያድጉ አራት እና አምስት ሺህ ዓመታት ብቻ ይበቃቸዋል፡፡

14520-races

የዳርዊን «የብቸኛ ዝርያዎች መንስዔ» (Origin of Species) የተሰኘ መጽሐፍ ታትሞ ከተሰራጨ በኋላ በሰዎች መካከል የዘረኝነት አመለካከት ከፊት ይልቅ እንደተባባሰ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ዝግመተ-ለውጠኞች እንደሚያምኑት የተለያዩ የሰው ዘር ነገዶች (races) ለብዙ መቶ ሺህ ዓመታት የየራሳቸውን የአዝጋሚ ለውጥ መስመር ተከትለው የመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ በሎጂካዊ አመለካከት የእነዚህ የተለያዩ ነገዶች የዝግመተ-ለውጥ ፍጥነት የተለያየ በመሆኑ ምክንያት አንዳንዶቹ ነገዶች በዝግተኛ የዝግመተ-ለውጥ ፍጥነታቸው የተነሳ ኋላቀር ሆነዋል፡፡ እነዚህ ኋላቀሮች ደግሞ ከሌሎቹ ይልቅ ከአሮጌው እንሰሳዊ የዘር ግንድ ጋር በጣም የጎላ ተቀራራቢነት አላቸው፡፡ ይህም አመለካከት አንዱን የሰው ነገድ ዓይነት ዘመናዊ ሌላውን ደግሞ ኋላቀር አድርጎ በመቁጠር በሰው መካከል የዘር ልዩነት እንዲፈጠር ክፍተትን ፈጥሯል፡፡

በተቃራኒው የዘመናዊው የሥነ-ባህርይ ሳይንስ ሁሉም የሰው ዘሮች በሥነ-ህይወታዊ ንጽጽር እጅግ በጣም የተቀራረቡ እንደሆኑና በባቢሉን ከነበረው የዘር ግንዳቸው ጋር ሙሉ የባህርይ ተዛምዶ እንዳሳቸው ያመለክታል፡፡

ለምሳሌ ብዙዎች በሰው ዘር ውስጥ የቆዳን ቀለም የሚወስን አንድ አቅላሚ ኬሚካል (coloring pigment) ብቻ እንዳለ ሲሰሙ ይደነቃሉ፡፡ አንድ ሰው የቆዳው ቀለም ጥቁር፣ ነጭ ወይም ቡናማ እንዲሆን የሚያደርገው በውስጡ ያለው ሜላኒን ተብሎ የሚጠራ አቅላሚ ኬሚካል መጠን ነው፡፡ ስለዚህ በዘመናዊው ሰው ዘር ውስጥ የሚታዩት የተለያዩ የተዳቀሉ ባህርያት በሙሉ በኖኅ ቤተሰብ /ከዚያም ቀደም በአዳምና በሄዋን/ ውስጥ ይገኙ ስለነበር ኖኅና ቤተሰቡ የእነዚህ ባህርያት ቅልቅል /ከፊል-ቡናማ የቆዳ ቀለም፣ ጥቁር ጸጉር እና ቡናማ የዓይን ቀለም/ እንደነበራቸው መገመት እንችላለን፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ቃየን መንድሙን አቤልን ከገደለ በኋላ ያገባት ሚስት የአዳም ዘር አልነበረችም የሜል አስተሳሰብ አለ፡፡ ታዲያ የአዳም ዘር ካልነበረች «የቃየን ሚስት ማን ነበረች?» የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ቢሆንም ይህ ጥያቄ የኅላዌ-ፈጣሪ አመለካከትን የሚቃወም ሳይሆን እንዲያውም የሚያጠናክረው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት 5.4 ላይ አዳም እና ሔዋን ሴቶች ልጆችም እንደነበሩአቸው ስለሚናገር የቃየን ሚስት ከእህቶቹ አንዷ እንደነበረች ይታመናል፡፡

በዚህም መሠረት በድንገለውጥ የሚነሱ እንከኖች ገና ከመነሻው ላይ ሳይሆን በትውልዶች ውስጥ ተከማችተው ስለሚሠሩ የአዳም ልጆች የቅርብ ዝምድና ጋብቻ ለብዙ ክፍለዘመናት የዚህ እንከን መዘዝ አያሰጋውም ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ አብርሃም እንኳን ግማሽ እህቱን በሰላም አግብቶ መኖር ችሷል፡፡ በተጨማሪም ይህንን የቅርብ ዝምድና ጋብቻ የሚከለክለው ድንጋጌ በሙሴ በኩል ለሰው የተሰጠው ከቃየን ዘመን ብዙ ዓመታት በኋላ ነበር፡፡

በእውኑ የሰው ዘር የኖኅን የጥፋት ውሃ ከመሰለ ታላቅ ዓለም አቀፍ መቅሰፍት ከተረፉ ሰዎች የመጣ ከሆነ «በትውልዶች አፈታሪክ ውስጥ ይህ ታሪክ ሰፊ ሥፍራ ሊይዝ አይገባውምን?» የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ በመሠረቱ የአውስትራሊያ አቦሪጂንስ፣ የአርክቲክ ኤስኪሞስ፣ የአሜሪካን ኢንዲያንስ እና በመላው ዓለም በሚገኙ አያሌ ነገዶች በሙሉ ስለ ጥፋት ውሃ የሚያወሳ ታሪክ በአፈታሪካቸው ውስጥ ተካትቶ ይገኛል፡፡

14575-chinese
ስዕል 11

ትረካው በጊዜ ብዛት እና በቅብብሎሽ ሂደት እየተዛባ ቢሄድም ከዘፍጥረት መጽሐፍ የአፈጣጠር ታሪክ ጋር ተመሳሳይነቱ የጎላ ነው፡፡ ለምሳሌም ያህል ኖኅ ቁራውን ከመርከቡ መላኩ እና ከጥፋት ውሃ በኋላ ይቀርቡ የነበሩ መስዋዕቶች ይጠቀሳሉ፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ ቀስተ ደመናውና ከአደጋው የተረፉት ሰዎች ቁጥር ስምንት መሆኑ እንኳን በትክክል ይጠ ቀሳል፡፡ ለምሳሌ የጥንታዊ ቻይናውያን የስዕል ቋንቋ «ጀልባ» ለሚለው ቃል የሚሰጠው ስዕላዊ መግለጫ ከጀልባ ምስል በተጨማሪ በውስጡ ስምንት አፎችን /ስምንት ሰዎችን ያመለክታል/ ያካትታል፡፡

በተጨማሪም በአንድ ጥንታዊ የፊደል ገበታ ላይ ሰፍሮ የተገኘ ጥንታዊ የመሰጴጦምያ የጎርፍ አፈታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካለው ታሪክ ጋር የተመሳሰለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል የማይቀበሉ አንዳንድ ቡድኖች በኖኅ ዘመን የተከሰተውን የጥፋት ውሃ ታሪክ መሰጴጦምያን ከመሳሰሉ ጎረቤት ህዝቦች እንደኮረጁት አድርገው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን የመሰጴጦምያ የጎርፍ አፈታሪክ ከሌሎች የአሜሪካ ኢንዲያንስን የመሳሰሉ በክልል ራቅ ያሉ ህዝቦች አፈታሪክ ጋር ሲነጻጸር የትረካው መዛባት ቦታው እየራቀ ስዕል 11 ሲሄድ አየጨመረ እንደሄደ ይመሰክራል፡፡

ብዙዎች ሌሎች ህዝቦች ደግሞ ከባቢሉን የቋንቋ መደበላለቅ ጋር የሚመሳሰል አፈታሪክ አላቸው። በአንፃሩ ግን ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጉልህ ሥፍራ የሚሰጠውን የቀይ ባህር መከፈል ታሪክ ብዙ አፈ ታሪኮች አይዘግቡም፡፡ ምክንያቱም ይህ የተከሰተው ከባቢሎን የቋንቋ መደበላለቅና መከፋፈል በኋላ ነበርና ነው። በዚህም ምክንያት ይህ ታሪክ በተወሰኑ ህዝቦች አፈታሪክ ውስጥ ብቻ ሊቀር ችሷል።

Mt Isa Mines14575-stalactites

የሬዲዮ አክቲቫዊ ዝመና (Radioactive Dating) ምድር ረጅም እድሜ እንዳላት አያረጋግጥምን?

በእርግጥ የዝግመተ-ለውጥ አመለካከትን በሚቃረን መልኩ ለምድር እና ለመላው ዩኒቨርስ ትንሽ እድሜ የሚሰጡ ብዙ የዝመና ዘዴዎች አሉ፡፡ አንዳንዶች ይህንን እድሜ ቢበዛ ከጥቂት ሺህ ዓመታት አይበልጥም ይላሉ፡፡ ቢሆንም ዝግመተ-ለውጠኞች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በተለያዩ ምክንያቶች የሚመርጡት የዝግመተ-ለውጥ አስተሳሰብን የሚደግፉ /የረጅም ዘመን እድሜ አስተሳሰብን የሚያራምዱ/ ዝመናዎችን ነው፡፡ ከእነዚህም አንዱና ዋነኛው የሬዲዮ አክቲቫዊ ዝመና ነው፡፡ እንዲያውም ፕሮፌሠር ሪቻርድ ሞገር የሚባሉ ዝግመተ-ለውጠኛ ሳይንቲስት እንደሚሉት «በአጠቃላይ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ግኝቶች ተብለው የሚቆጠ ሩትና ለህትመት የሚበቁት ምርምሮች ዝግመተ-ለውጣዊ ዝመናዎችን የሚቀበሉት ናቸው፡፡» ስለዚህ ካለው የ«ረጅም ጊዜ እድሜ» አመለካከት ጋር ግዴታ መጣጣም አለባቸው» ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ምንም እንኳን ፍጹም ስህተት ቢሆንም ሌላው በስፋት የሚታወቅ እምነት «ሁሉም ሬዲዮ አክቲቫዊ ዝመናዎች እርስ በርሳቸው ይስማማሉ» የሚለው አስተሳሰብ ነው፡፡

ለምሳሌ በኒውዚላንድ አገር በሚገኝ ራንጊቶቶ በሚባል ሥፍራ በገሞራ ትፍ (lava) ተቀብሮ የተገኘ እንጨት የካርቦን ዝመና ዘዴ እንዳመለከተው ፍንዳታው የተካሄደው ከ200 ዓመታት በፊት ገደማ እንደነበረ ነው፡፡ ነገር ግን በፓታሲየም አርጎን የዝመና ዘዴ ይኸው ገሞራትፍ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርስ እድሜ እንዳለው ተገምቷል፡፡

Rod Walsh14520-waterwheel1
Rod Walsh14520-waterwheel2
በምዕራባዊ አውስትራሊያ በኬፕ ሌዊን የሚገኝ የውሃ መዘውር (waterwheel) 65. ዓመት ባልሞሳ ጊዜ ውስጥ በጠጣር ዓለት ተቀብሮ ይታያል፡፡

ዳይኖሶሮች የዝግመተ-ለውጥ አመለካከትን እውነተኛነት ያረጋግጣሉን?

ብዙ ባህሎች ድራጎንን5 (dragon) የተመለከተ አፈታሪክ አላቸው፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ አስበን ይሆናል፡፡ እነዚህ ድራጎኖች ቀንዳም፣ ቅርፍ (scale) ያላቸውና ብረት ለበስ እንሰሳት እንደሆኑ ሲነገር አንዳንዶቹ ደግሞ መብረር ሁሉ የሚችሉ እንደነበሩ ይተረካል፡፡ ይህም ትረካ በቅሬተ-አካል ጥናት ከሚታወቁት ዳይኖሶሮች እና ሌሎች ውድም (extinct) የተሳቢ ዝርያዎች ጋር ከፍተኛ ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሆኖም ግን ማንም ሰው ዳይኖሶሮችንም ሆነ እነዚህን ጭራቆች አይቷቸው እንደማያውቅ ይኸው የዝግመተ-ለውጥ ንድፈሃሳብ ይነግረናል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስም ግን ድራጎን በሂብሩ ቋንቋ ታኒን እየተባለ ተጠቅሷል፡፡ ዳይኖሶር የሚለው ስያሜ በጥቅም ሳይ መዋል የጀመረው ከአሥራዘጠ ነኛው ክፍለዘመን በኋላ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳለ ከተቀበልን «ሰው እና ዳይኖሶሮች ከብዙ ዘመናት በፊት በአንድ ወቅት በጋራ ይኖሩ ነበር» የሚለውን አስተሳሰብ መቀበል አያዳግተንም፡፡ ባለፉት ዘመናት ብዙ ፍጥረታት ወድመዋል ጠፍተዋል፡፡ ይህ ውድመት ደግሞ አሁንም እየተከሰተ ይገኛል፡፡ ውድመት ማለት ግን ዝግመተ-ለውጥ ማለት አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ ዳይኖሶሮች ከሌሎች ፍጥረታት በዝግመተ-ለውጥ እንደመጡ የሚያሳይ የቅሬተ-አካል መረጃ የለም፡፡

ህይወት በአጋጣሚ?

14520-dinosaur

የዝግመተ-ለውጥ አስተሳሰብ በመጀመሪያ እንዴት እንደተጀመረ አስቀድመን እንመልከት፡፡ ዝግመተ-ለውጥ በብዙዎች ዘንድ የተረጋገጠ ሀቅ እንደሆነ ቢታመንም ቅሉ እንደእውነቱ ከሆነ የመጀመሪያውን ኢምንት «ሀይወት ያለው ነገር» ያስገኙት ውስብስብ እና መረጃ የተሞሉ ሞሌኪዩሎች እንዴት ያለምንም ውጫዊ ጥበብና ኃይል እንደተገኙ የሚያስረዳ ምንም ሳይንሳዊ እውቀት የለም፡፡ በአንጻሩ ይህ ዝግመተ-ለውጣዊ ንድፈሃሳብ ትክክለኛ እንዳልሆነ የሚገልጹ ጥሩ ሳይንሳዊ መረጃዎች አሉ፡፡

በአንድ ተሽከርካሪ ላይ የሚገኙ ቁሳቁሶች /ጎማ፣ ብረት፣ ፕላስቲክ ወዘተ/ በራሳቸው ተሽከርካሪውን እንዲንቀሳቀስ አያደርጉትም፡፡ መኪና የገንቢ ቁሶች መገጣጠምና የጉልበት ውጤት ብቻ ሳይሆን የማይታይ ቁስ አልባ መረጃም /እውቀት/ ውጤት ነው፡፡

ሌላ ምሣሌ ለማየት ያህል በዚህ ገጽ ላይ የተጻፉት ነገሮች የብዕርና የወረቀት ውጤት ብቻ ሳይሆኑ የመረጃ /እውቀት/ ጭምር ውጤቶች ናቸው፡፡ ወረቀቱና ብዕሩ የመረጃው ማስተላለፊያ መንገዶች ብቻ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ አንድን ህዋስ በውስጡ የያዛቸው ገንቢ ቁሶች ብቻቸውን «ሕያው» ሊያሰኙት አይችሉም፡፡ አለበለዚያማ በሰርዲን ውስጥ የተቀመጠ የአሣ ጉምድማጅ በአዝጋሚ ለውጥ ወደ ሕያውነት መቀየር በቻለ ነበር፡፡ ገንቢ ቁስ ኖሮ ጉልበት ቢታከልበት እንኳን ህይወትን መፍጠ ር አይቻልም፡፡ ከሁሉ በላይ አስፈላጊው ነገር መረጃ ወይም እውቀት ነው፡፡ ህይወት ያላቸው ነገሮች ይህንን መረጃ የሚያገኙት ከወላጆቻቸው ነው፡፡ ነገር ግን ይሀ መረጃ ዝም ብሎ ከማንኛውም ቁስ ሲገኝ ታይቶ አይታወቅም፤ አይቻልምም፡፡

በአዝጋሚ ለውጥ ሂደት ራሱን በራሱ ማራባት የሚችል ፍጥረት እስኪፈጠ ር ጊዜ ድረስ ዝግመተ-ለውጣዊ የምርጦሽ ሂደቶች ምን ዓይነት ሚና እንደተጫወቱ ለመግለጽ አዳጋች ነው፡፡ ዳሩ ግን ህይወት መረጃ የተሸከሙ ውስብስብ ኬሚካሎች (polymers) ውጤት ነው፡፡ እነዚህም በላያቸው ባሉ ንዑሳን ኬሚካሎች የአቀማመጥ ቅደምተከተል መሠረት ተግባራቸው የተወሰነ ረጃጅም ሰንሰለታማ ኬሚካሎች ናቸው፡፡

የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ግን ይህ መረጃ በድንገት የመጣ ነው የሚል አስተሳሰብ ያራምዳል፡፡ ሰር ፍሬድ ሆይል የተባሉ ሰው በአመለካከታቸው ምንም እንኳ ኅላዌ-ፈጣሪያዊ | ባይሆኑም «ዝግመተ-ለውጥ ከጠፈር» (Evolution from space) በሚለው መጽሐፋቸው እንደገለጹት አንድ ዓይነት ውስብስብ ኬሚካል በአጋጣሚና በነሲብ የሚፈጠርበት እድል እጅግ እጅግ በጣም ኢምንት እና የማይታሰብ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ታዲያ ብዙዎች የዝግመተ-ለውጥ አመለካከትን በግትርነት የሚከተሉበት ምክንያት ምንድነው?

ለዚህ ጥያቄ ብዙ ምክንያቶች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል እንደ ማኅበራዊና ባህላዊ ጫና፣ ሌሎች አማራጮችን ለመማር አለመታደል፣ እና የት/ቤቶች የሥርዓተ-ትምህርት ሁኔታ ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ የዚህም ምንጭ የሰው ዘር በአዳም መተላለፍ ምክንያት ከክብሩ ከወደቀ በኋላ የፈጣሪን ትዕዛዞች የመቃወምና የመጣስ ደመነፍሳዊ ዝንባሌ ማዳበሩ ነው፡፡ ስለዚህ የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት አራማጅ ከሆኑ እነዚህን ከላይ በአጭሩ የተቀመጡ ነጥቦች ልብ ይበሉ፡፡ ለህይወት ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖርዎት ይህ አንድ ትልቅ እርምጃ ነውና፡፡

ሮሜ ምፅራፍ 1 ቁጥር 18–22 ያንብቡ፡፡

ማጣቀሻዎች እና ማስታወሻዎች

  1. የዝግመተ-ለውጥ አመለካከት ዓለምና በውስጧ ያሉ ህያዋን ሁሉ ያለምንም መለኮታዊ ኃይል አስተዋፅኦ ረጅም ጊዜን በወሰደ አዝጋሚ ለውጥ እንደተገኙ ሲያስተምር የኅላዌ-ፈጣሪ አመለካከት ግን ዓለምና ሞላዋ ሁሉ በመለኮታዊ ኃይል እንደተፈጠሩ ያስተምራል፡፡ ወደ ጽሑፍ ተመለስ.
  2. ቢቨር /ገድቤ አይጤ/ በምድርም በውሀም ውስጥ መኖር የሚችል አይጦቾ ከሚገኙበት መደብ (rodents) የሚመደብ እንሰሳ ነው፡፡ ወደ ጽሑፍ ተመለስ.
  3. ኤፕ ተብሎ የሚጠራው የእንሰሳት ቡድን ዝንጀሮም ጦጣም አይደለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ አራት የኤፕ ዝርያዎች በምድር ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም chimpanzee፣ gorilla፣ orangutan እና gibbon ተብለው ሲጠሩ በአፍሪካ አህጉር የሚገኙት ግን የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ብቻ ናቸው፡፡ ወደ ጽሑፍ ተመለስ.
  4. አብዛኞቹ የሰው ህዋሶች በውስጣቸው 23 ጥንድ ክር መሰል ነገሮች /ክሮሞዞም/ አላቸው፡፡ እነዚህ ክር መሰል ነገሮች በላያቸው DNA /deoxyribonucleic acid/ የሚባሉ የሰውን ባህርይ የሚወስኑ ኬሚካሎች አሳቸው፡፡ ወደ ጽሑፍ ተመለስ.
  5. ድራጎን ለሚለው ቃል ትክክለኛ ተመሳሳይ የአማርኛ ቃል ስላላገኘሁ እንዳለ አስቀምጨዋለሁ፡፡ ወደ ጽሑፍ ተመለስ.